Fana: At a Speed of Life!

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ከመራጩ ሕዝብ 98 ከመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል።
በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ሰዎች 215 ሺህ እንደነበር ተዘግቧል።
ምርጫውን በበላይነት የመሩት የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሙሚን አሕመድ ሼክ አርብ ዕለት 167 ሺህ 535 መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ ይፋ በተደረገው ጊዜያዊ ውጤት መሠረትም ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ከ98 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ተገልጿል።
ብቸኛው ተፎካካሪያቸው የነበሩት ዛካሪያ ኢስማኢል ፋራህ 1ነጥብ 59 በመቶ ብቻ የመራጮችን ድምጽ ማግኘታቸውም ነው የተገለጸው።
ገለልተኛ የምርጫ ታዛቢዎች ሥነምግባር የጎደለው ሪፖርት አለመኖሩንና የምርጫ ሂደቱ ያለችግር እንደተካሄደ ገልጸዋል፡፡
የ73 ዓመቱ ኤስማኤል ጊሌ እንደ አውሮፓውያኑ ከ1999 ጀምሮ ጂቡቲን በፕሬዝዳንትነት በመምራት ላይ ይገኛሉ።
ኤስማኤል ጊሌ የዘንድሮውን ምርጫም በከፍተኛ ውጤት ማሸነፋቸው ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት ጂቡቲን እንዲመሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
በቆዳ ስፋት አነስተኛ የሆነችውና በአፍሪካ ቀንድ ቁልፍ አካባቢያዊና ወታደራዊ ቦታ የያዘችው ጂቡቲ ጠቅላላ የሕዝብ ብዛቷ ከአንድ ሚሊየን ያነሰ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ምንጭ፡- አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.