Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር 450 ሚሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 450 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን እና በ2014 517 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ሂርሲ አብዲ ለሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን እንደገለፁት፥ በከተማው በ2013 የበጀት አመት ስድስት መቶ ዘጠኝ ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ አራት መቶ ሀምሳ ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል።

ኃላፊው በ2013 የበጀት አመት ከእቅዱ አንፃር በከተማው የተሰበሰበው ገቢ መቀነስ የህብረተሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆንና በገቢ አሰባሰብ ስራዎች ላይ በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ በኩል የነበሩ ያለመናበብ ችግሮችን በምክንያትነት አንስተዋል፡፡

በከተማው በ2013 የበጀት አመት በገቢ አሰባሰብ ላይ ያጋጠሙ ክፍተቶችን በማሻሻል ጠንካራ ስራዎችን በማጎልበት በ2014 የበጀት አመት አምስት መቶ አስራ ሰባት ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው የተናገሩት፡፡

በከተማው የሚገኙ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትና በህብረተሰቡ ዘንድ ግብር የመክፈል ግዴታና ያለው ጠቀሜታ ዙሪያ ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።

የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ግብር መክፈል ለክልሉም ይሁን ለሀገሪቱ ልማትና እድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ ያለባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ ማሳሰባቸውን ከሶማሌ ብዙሃን መገናኛን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.