Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 200 የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 32 የሕክምና ዶክተሮችን ጨምሮ 200 የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ካሰለጠናቸው 32 የሕክምና ዶክተሮች  መካከልም 10ሩ ሴት የሕክምና ዶክተሮች ናቸው።

በአጠቃላይ ዛሬ ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 109ኙ ወንዶች ሲሆኑ 91ዱ ደግሞ  ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርስቲው ሲቋቋም 700 የሚጠጉ ተማሪዎችን በመቀበል የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ የመቀበል አቅሙን ከ25 ሺህ በላይ ማድረሱን የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ አወሎ አብዶ በበኩላቸው ዓድዋ ላይ ያሸነፈውን ኢትዮጵያዊነት እና ከአባቶቻችን የወረሳችሁትን የድል አድራጊነት መንፈስ በመድገም በምትሠማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ በትጋት መሥራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ለተመራቂ ተማሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው ለሀገር እና ሕዝብ የገቡትን ቃለ-መሃላ በመጠበቅ ሕዝባቸውን በዕውቀት እና በኃላፊነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን እንደተናገሩ ኢብኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.