Fana: At a Speed of Life!

የጆ ባይደን አስተዳደር ለፍልስጤም የ235 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለፍልስጤም ተቋርጦ የነበረውን ድጋፍ ለማስቀጠል የ235 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
የአሁኑ ድጋፍ በ75 ሚሊየን ዶላር በዌስት ባንክ በጋዛ ሰርጥ የሚደረግ የኢኮኖሚና የልማት ድጋፍን ያካተተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብለኪንከን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት ለሰላም ግንባታ የሚውል 10 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን፥ የፀጥታና ደህንነት ድጋፍም ዋሽንግተን ታደርጋለች ተብሏል፡፡
ድጋፉ አሜሪካ በዌስት ባንክና ጋዛ ሰርጥ ከኮቪድ 19 እና ምግብ ዋስትና ጋር በተያያዘ ባለፈው ወር ካደረገችው 15 ሚሊየን ዶላር በተጨማሪነት የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ከታቀደው ድጋፍ ውስጥ 2/3 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
ኤጀንሲው ከፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ በአሜሪካ በተቋረጠበት የ360 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሳቢያ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አጋጥሞታል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.