Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር በህዳር ወር 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በህዳር ወር 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 የንቅናቄ ስራዎች በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተፈጠረዉ ግንዛቤ የግብር ጉዳይ የህዝብ አጀንዳ በመሆኑ የገቢ አሰባበሰቡ ከመቼዉም በተሻለ መልኩ እድገት እያሳየ መሆኑን ገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት በህዳር ወር 18 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው ያስታወቀው፡፡

አፈጻጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ5 ነጥብ 97 ቢሊየን ብር ወይም የ36 ነጥብ 14 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የገቢዎች ሚኒስቴር አመራር፣ ሰራተኛዉና የንግዱ ማህበረሰብ በጋራ የሰሩት ስራ ለዉጤቱ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ባለፉት አምስት ወራት እያስመዘገበ ያለዉ የገቢ አሰባሰብ ዉጤት አበረታችና ስኬታማ መሆናቸዉ የአመቱን እቅድ ለማሳካት ማሳያዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.