Fana: At a Speed of Life!

የገዳ ስርዓት በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበት 4ኛ ዓመት በጉጂ ዞን ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበበት 4ኛው ዓመት በጉጂ ዞን ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፥ የጉጂ ዞን እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉን በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

በፕሮግራሙ የገዳ ስርዓት በማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገበ ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት ይገመገማሉ።

ምሁራን የመወያያ የጥናት ጽሁፎችን የሚያቀርቡ ሲሆን፥ አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ልምዶቻቸውን ያካፍላሉ ብሏል የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ።

ይህ ሀገር በቀል ስርዓት በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበ አራት ዓመት ሆኖታል።

ገዳ በቅርስነት ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ የስርዓቱን ትውፊት እና እሴቶች አዳብሮ ለትውልድ ለማስተላለፍ ክልሉ በየአመቱ ሁነቱን በተለያዩ ፕሮግራሞች እያከበረ ይገኛል።

መድረኩም ዛሬ ጥር 1 እና 2 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ ትዕይንቶች ይከበራል፡፡

ክልሉ ከስርዓቱ የመነጨው የግብረ ገብነትና የበጎ ፈቃድ የዜግነት አገልግሎትን ስራ ላይ እንዲውል እና ገዳ በትምህርት እንዲሰጥ በተግባር እየሰራ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

ገዳ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና ምንጭ መሆኑ ይታወቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.