Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ስርዓትን ለማሻሻል የሚያግዝ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን አሰራሩን ቀልጣፋ፣ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ አስተዋፅኦ እንዳለው የታመነበት ስምምነት ከኢትዮጵያ ፍራይት ፎርዋርደርስ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶስሽን ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እና የማህበሩ የቦርድ ሊቀመንበር ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፥ ስምምነቱ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት አፈፃፀም እንዲሁም በሎጅስቲክስ አገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙ እና ሌሎች ክፍተቶችን ይቀርፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
በቅንጅት በመስራት ምቹ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ የሎጅስቲክስን ተወዳዳሪነት ከፍ በማድረግ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ቀረጥና ታክስ ለመሰብሰብ እንደሚያግዝ ደግሞ የማህበሩ የቦርድ ሊቀመንበር ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር የሕግ ተገዥነት ሥርዓትና ባህል እንዲዳብር ለማድረግ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል መጠቆማቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.