Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ኮሚሽን ለመከላከያ ሰራዊት የ28 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት 20 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 8 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

በድጋፉ ወቅት ንግግር ያደረጉት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፥ ኮሚሽኑ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የህልውና ዘመቻው ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ 160 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ከ78 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፥ ዛሬም 8 ሚሊየን ብር የሚያወጡ አልባሳትን እና 20 ሚሊየን ብር ለሰራዊቱ ድጋፍ መደረጉንም ነው የገለጹት፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጅ በበኩላቸው፥ መላው ኢትዮጵያውያን ለህልውና ዘመቻው ያደረጉት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ዛሬ ለተገኘው ድል ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት ያሳየውን ፍቅር እና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.