Fana: At a Speed of Life!

የጉሮሮ እብጠትን መለየት የሚችል ሮቦት ወደ ሙከራ ገባ

 አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በቻይና በቫይረሱ እንዳይጠቁ ለማድረግ የጉሮሮ እብጠትን መለየት የሚችል ሮቦት ወደ ሙከራ ገብቷል፡፡
አሁን ላይ ለአለም ስጋት የሆነው የኮሮና ቫረስን ለመግታት ሃገራት ርብርብ እያደረጉ ትገኛሉ፡፡
ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታት አለመጠቃታቸውን ለማረጋገጥ የጉሮሮ እብጠት ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ስራውን ለማገዝም ሮቦቶች ሰውን ተክተው የተለያ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በቻይናም የህክምና ባለሞያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ እነሱን ተክቶ የጉሮሮ እብጠትን መለየት የሚችል ሮቦት ወደ ሙከራ አስገብተዋል፡
የጉሮሮ እብጠትን መለየት ከታማሚው ጋር ቅርርብ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህም ከታማሚ ወደ ባለሙያ የቫይረስ መተላለፍ እድልን ያሰፋል፡፡
ይህን ለመቅረፍም ሮቦቱ በተሰራለት ክንድ ፣ በአቅራቢ መነፅር እና ገመድ አልባ ማሰራጫ መሣሪያዎች በመጠቀም መረጃውን ይሰበስባል፡፡ በዚህም የህክምና ሰራተኞች ሂደቱን በርቀት መቆጣጠር ይችላሉ ነው የተባለው ፡፡
በቻይና የሳይንስ አካዳሚ በሚመራ ቡድን የተሰራው ሮቦት የህክምና ባለሙያዎችን ከበሽታ ለመከላከል እና የባዮሎጂካል ናሙና ስብስብ ትክክለኛነት ለማሻሻል ታስቦ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሮቦቱም ጉሮሮ ሳይጎዳ የጉሮሮ እብጠቶችን ከ95 በመቶ በላይ መሰብሰብ ይችላል ነው የተባለው ፡፡
ምንጭ፡-ሲጂቲኤን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.