Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ1 ሺህ 151 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማደረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ1 ሺህ 151 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየገመገመ ነው፡፡
በዚህ ወቅት ባለፉት 10 ወራት ከክልሉ ለብሔራዊ ባንክ 1 ሺህ 330 ኪሎ ግራም ወርቅ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ 1 ሺህ 151 ኪሎግራም ከ700 ግራም ወርቅ ገቢ መደረጉ ተገልጿል።
ገቢ የተደረገው ወርቅ በዲማ፣ በአበቦና ጋምቤላ ወረዳዎች በባህላዊ ወርቅ አምራቾች የተመረተ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ባለፉት 10 ወራት የተገኘው የወርቅ ምርት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ211 ኪሎ ግራም በላይ ብልጫ እንዳለው ተመልክቷል።
ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ከተደረገው የወርቅ ምርት ከ59 ሚሊየን 400 ሺህ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንደሚገኝ ይጠበቃልም መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.