Fana: At a Speed of Life!

የጋሞ ልማት ማህበር ከ39 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ተግባራት አከናውኗል

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የጋሞ ልማት ማህበር በ9 ወራት ከ39 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ተግባራት ማከናወኑ ተገለፀ፡፡

የልማት ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ትግሉ ኃይሌ÷ በ 9 ወራት ልማት ማህበሩ ቁልፍ የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በቅርንጫፍ እና በዋናው ልማት ማህበር 39 ሚሊየን 85 ሺህ 245 ብር ወጪ የተለያዩ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል ።

በትምህርት ልማት ፣ በጤና ዘርፍ ፣ በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ፣ ለመንገድ ልማት ፣ለባህልና ቱሪዝም ድጋፍ ማድረግ የከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውም ተገልጿል ።

በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ከሆኑ ቤተሰብ ዓባላት የተገኙ እና ወላጅ አጥ የሆኑ 64 ተማሪዎች በ9 ወራት ድጋፍ ተደርጎላቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙም ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.