Fana: At a Speed of Life!

የጋሞ ዞን ሕዝቦች ዘመን መለወጫ ዮ ማስቃላ በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጋሞ ዞን ሕዝቦች ዘመን መለወጫ ዮ ማስቃላ በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የዞኑ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘነበ በየነ እንዳሉት የጋሞ ሕዝቦች ማስቃላ በዓል በአለም ቱሪስቶች የሚጎበኝ ለማድረግ በመንከባከብ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት መኖሩን የተናገሩት አቶ ዘነበ ይህም የሆነው በጋሞ አባቶች ጥረት ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የጋሞ ዞን ሰላም በመሆኑ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ98 ሚሊየን ብር በላይ መገኘቱን ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መረጃ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው ዞኑ የበርካታ የቱሪስት መስህቦች መገኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰላም ሲጠበቅ ባህል፣ ወጎች፣ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህቦችን ለአለም ሕዝብ እንዲተዋወቅ እድል በመፍጠር ፤ዘርፉ ለዞኑ ኢኮኖሚኖሚ ማህበራዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.