Fana: At a Speed of Life!

የጋና የፓርላማ አባላት ፓርላማው በጊዚያዊነት እንዲዘጋ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የጋና የፓርላማ አባላት ፓርላማው በጊዚያዊነት እንዲዘጋ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጋና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ውስጥ ሁለት የፓርላማው አባላት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ በኋላ ፓርላማው በጊዜያዊነት እንዲዘጋ መጠየቃቸው ተነግሯል።

ምርመራ ከተደረገላቸው የፓርላማ አባላት እና የምክር ቤቱ ሰራተኞች መካከል ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና 15 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

በዚህም ምክንያት በርካታ የፓርላማው አባላት በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ በሚል አብዛኛው የምክር ቤቱ አባላት የፓርላማው ስብሰባ በሌላ አማራጭ እንዲካሄድ ጠይቀዋል፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ከ200 ሺህ በላይ የኮቪድ-19 ምርመራዎችን ያካሄደች ሲሆን፥ እስካሁን ባለው መረጃ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ34 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.