Fana: At a Speed of Life!

የጋፋት የልማት ሥምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታሪካዊውን ጋፋት የኢንዱስትሪ እና የጥበብ መንደር ለማልማት የሚያስችለው የስምምነት ፊርማ ሥነ ሥርዓት በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መካከል ተከናውኗል።

ስምምነቱም ጋፋት ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ የጎብኚዎች መዳረሻ እንዲሆን ለማድረግ እና ለትውልድ ማስተላለፍ ያስችላል ተብሏል።

ጋፋት ከደብረ ታቦር ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው።

በዚህ ስፍራ ከጥንት ጀምሮ የብረታ ብረት፣ ሸክላ እና ሌሎች የእደ ጥበብ ሙያ የነበራቸው ሰዎች ይኖሩበት ነበር፡፡

በአካባቢው ያለውን የብረት ማዕድን ምክንያት በማድረግም አፄ ቴዎድሮስ በ1850ዎቹ የሀገር ውስጥ የእጅ ጥበበኞችን እና የውጭ ሃገር ሚሲዮናውያንን በማሰባሰብ ሴባስቶፖል መድፍን ያሰሩበት ታሪካዊ ቦታ ነው።

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢንዱስትሪ መንደር እና ወታደራዊ ትምህርት ቤት እንደተጀመረበትም ይነገራል፡፡

ይሁን እንጅ ይህ ታሪካዊ ቦታ ታሪካዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲቆይ ባለመደረጉ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበት ቆይቷል፡፡

ቦታውን አልምቶ በመጠበቅ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እና ለትውልድ ለማስተላለፍ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መካከል የሦስትዮሽ ትብብር ስምምነት ፊርማ ሥነ ሥርዓት መከናወኑን አብመድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.