Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ዳራሮና የምስጋና በዓል መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ዳራሮና የምስጋና በዓል የገዳ ሥርዓቱ መቀመጫ በሆነው ቡሌ ወረዳ አጋምሳ ቀበሌ ኦዳ ያአ ላይ መከበር ጀምሯል፡፡
የጌዴኦ ብሄር የገዳ መሪ ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት ዳብሮ ከትዉል ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ በጥልቀት ሊሰራበት እንደሚገባ የደቡብ ከልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ፡፡
የቡሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በራቆ በራሶ ÷የጌዴኦ ብሄር በራሱ ባህላዊ ሕግ በመመራት ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውን ሥርዓት የዛሬው ትዉልድ ሲያከብር ትዉፊቱን ወጉንና ሥርዓቱን የማስቀጠል አደራ አለበት ብለዋል፡፡
መገፋፋትና ጥላቻን በመተው በአንድነት በድህነት ላይ የተጀመረውን የልማትና የዕድገት ዘመቻ ዉጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ዳራሮ በዓመቱ ካገኘነው ምርት ለአባ ገዳ ስጦታ ስናቀርብ የምንባረክበትና ባህል ታሪክና ትዉፊታችን ነው ብለዋል
በመሆኑም ይህ ትውፊታችን ተከብሮና ተጠብቆ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በማሸጋገር በአለም የቅርስ መዝገብ ላይ ለማስመዝገብና ይህ የአደባባይ በዓላችንም የአለም ሃብት እንዲሆን ልንጠብቀውና ተግተን ልንሰራም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
የጌዴኦ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ እጩ ዶክተር ዮሴፍ ማሩ በበኩላቸው ÷ የጌዴኦ ብሄር ከጥንት ጀምሮ የራሱን ወግና ሥርዓት ለማስቀጠል ሳይፃፍ ነገር ግን ሳይዛነፍ ወደ ትዉልድ እያሸጋገረ የመቆየቱ ምስጢር መገለጫው ዳራሮና ይህ የምስጋና ሥርዓት ነው ብለዋል፡፡
ዳራሮን ስናከብር በጋራ አደባባይ እንደወጣን ሁሉ ያለንን ጉልበት እዉቀትና ሓብት ወደ ልማት በመቀየር በህዝባችን ዉስጥ የሚስተዋሉ የልማትና የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን የምንፈታበት ሊሆን እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሺፈራ ቦጋለ÷ የጌዴኦ ብሄር ከሌላው ሕዝብ ለየት የሚያደርገው ሕዝቡ የሰፈርበት ቦታ ተዳፋታማና ተራራማ ቢሆንም ለምለምና ምርታማ ሆኖ እንዲቀጥል ያደረገው የገዳ ሥርዓት አንድ አካል የሆነው የደን አያያዥ አፈርና ዉሃ አጠባበቅ ቱባ ባህልና ወጉ በመሆኑ ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ትዉልድ ከአሉባልታ ከፀረ- ሰላም ኃይሎች አላማና ተልዕኮ ራሱን ነፃ በማዉጣት መንግስት የጀመረውን የለውጥና የልማት ተግባራትን ማገዝ እንደሚጠበቅበትም ጠቁመዋል፡፡
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ÷የጌዴኦ ብሄር ተጠንቶ ተመርምሮ የማያልቅ ባህልና ወግ ያለው ሕዝብ ነው ብለዋል።
የጌዴኦ ብሄር በየ 8 ዓመቱ በዴሞክራሲ ሥርዓት የገዳ ምርጫ በማካሄድ ያለ አንዳች ችግር ባህላዊ መሪውን በመምረጥ የዴሞክራሲ ሥርዓትን ያዳበረው ሕብረተሰቡ ነባር ዴሞክራሲያዊ እሴቱን ጠብቆ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር አብሮ የመኖር ባህሉን በማዳበር በመከባበር በመነጋገር በመተጋገዝ ያሉብንን ችግሮች በጋራ በመፍታት ሕዝባችንን ማሸገር ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር እንደሆነም መናገራቸውን ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.