Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴንና ኢ/ር ታከለ ኡማ ለከተማ ግብርና የተለዩ ቦታዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለከተማ ግብርና የተለዩ ቦታዎችን ጎበኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ የከተማ ግብርናው ሀሳብ ነዋሪዎች ባላቸው ክፍት ቦታ ላይ በመጠቀም ለምግብነት አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያመርቱ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ የከተማ ግብርና በከተማዋ በተለያየ ወቅት የሚፈጠሩ እጥረቶችንም ለመቅረፍ ይረዳልም ነው ያሉት።

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን በበኩላቸው፥ ሚኒስቴር መስሪ ያቤቱ ለከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በቅርቡ ይፋ በተደረገው የከተማ ግብርና ፕሮጀክት ከ100 በላይ ቦታዎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል።

በዘርፉ ወጣት ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ጥሪ በቀረበው መሰረትም በኦንላይን ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የከተማ ግብርና ፕሮጀክቱ በተለይም በከተማዋ የሚገኙ የወንዝ ፍሰቶችን በመከተል የሚተገበር እንደሚሆንም ተመላክቷል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.