Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን የመተካት ሙሉ አቅም እንዳላቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ምርትን የመተካት ሙሉ አቅም እንዳላቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ እሸቴ አስፋው ተናግረዋል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአማራ ክልል የንግድና ገበያ ለልማት እንዲሁም ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮዎች አመራሮች በቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ የገቡ ፋብሪካዎችንና ፊቤላ የዘይት ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ 97 በመቶ የግንባታ ስራው በተጠናቀቀው የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ በ7 የምርት አይነቶች የተሠማራው ሪችላንድ አግሮ ኢንዱስትሪና በዘይት ማምረትና የአልሚ ምግብ ዘርፍ የሚሠራው የቻይና ኩባንያ ወደ ስራ መግባታቸው ተገልጿል።

በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የኢንቨስትመንት ወጪ ወደ ስራ እየገባ የሚገኘው እና በቀን 1 በጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይት በማምረት የሀገሪቱን የዘይት ፍላጎት 60 በመቶ እንደሚያሟላ የተነገረለት የፊቤላ የምግብ ማቀነባበሪያና የዘይት ፋብሪካም ተጎብኝቷል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩና በዘይት ፋብሪካው የኃይል አቅርቦት ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትና በሀገር ውስጥ የግብርና ግብአቶች አቅርቦት ውስንነት ዘርፉን ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች ለመተካት የተያዘውን እቅድ በተሟላ እንዳይፈፀም እያደረጉ ያሉ ተግዳሮቶች እንደሆኑም ተመላክቷል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው የአካባቢውን ፋብሪካዎች መሸከም የሚችል የኃይል ማከፋፈያ ንዑስ ጣቢያ ለመገንባት ስራዎች እየተጠናቀቁ በመሆናቸው ችግሩ እንደሚቃለል ተናግረዋል።

ከመደበኛ የመኸር ምርት ባለፈ መስኖን በማጎልበት የምርት አቅርቦትን ለማሳደግ፣ ከውጭ ዘይት ይገባበት የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ወደ አልሚዎች በማስተላለፍ የምንዛሬ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ እንደሚሠራ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.