Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ዘርፍ የወጪ ንግድ አፈፃፀም የእቅዱን 109 በመቶ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት ከግብርናው ዘርፍ የውጨ ንግድ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የግብርና ሚኒስተር አስታወቀ::

ይህም አፈፃፀም የዕቅዱ 109 በመቶ መሆኑን ነው ያመለከተው።

ይህ ከባለፈው አመት የ6 ወር አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ323 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፥ ማለትም 32 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው።

በዚህም ግብርናው ከሀገራዊ አፈፃፀሙ 70 በመቶ ድርሻ እንደነበረው ያመላክታል ነው የተባለው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሂደቱ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ሁሉ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፥ በቀጣይ 6 ወራትም ተጠናክሮ እንደቀጥል መጠየቁን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.