Fana: At a Speed of Life!

የግብጽ ሰብዓዊነት የጎደለው የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲይ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የግብጽ ሰብዓዊነት የጎደለው የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

አምንስቲ ኢንተርናሽናል በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ የአረብ አብዮት ከተከሰተ ከ10 ዓመት በኋላ የግብጽን የእስረኞች አያያዝ ተችታል፡፡

የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዳስታወቁት ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊነት በጎደለውና በተጨናነቁ እርስር ቤቶች መታሰራቸውንም ነው የገለጹት፡፡

እስረኞቹ በጨለማ ቤት ውስጥ፣ ንጹህ አየር በማያገኙበት እና ንጽህናቸው ባልተጠበቁ መጸዳጃዎች ውስጥ እንደሚጠቀሙ ነው አምንስቲ የገለጸው፡፡

ይህ ሰብዓዊነት የጎደለው አያያዝም በእስረኞች ላይ አላስፈላጊ ስቃዮች እንዲጋፈጡና አንዳዶቹም ህይወታቸውን እንዳጡ ነው ይፋ ያደረገው፡፡

እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት ሁኔታ ያለመኖሩ እንዲሁም ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ወጥነት የሌለው አሰራሮች መንሰራፋታቸውን በሪፖርቱ አትቷል፡፡

በተጨማሪም በእስረኞች ላይ ለ20 ሰዓታት የሚዘልቅ ስቃይ እንደሚደርስባቸውም ተገልጿል፡፡

የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ጥናት ያተኮረው በሀገሪቱ በሚገኙ 16 እስር ቤቶች ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

እንደተባበሩት መንግስታት መረጃ ከሆነ በግብጽ እስር ቤቶች ውስጥ 114 ሺህ ታራሚዎች መኖራቸውን ያመላክታል፡፡

ምንጭ፦አልጀዚራ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ምንጭ፦አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.