Fana: At a Speed of Life!

የግድቡ 3ኛ የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ግንባታውን አትጨርስም ለሚሉ ወገኖች ምላሽ የሰጠ ነው – መሀመድ አል አሩሲ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 3ኛ ሙሌት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ስኬት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአባይ ግድብ ተሟጋች መሀመድ አል አሩሲ ተናገሩ፡፡

አል አሩሲ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፥ የግድቡ 3ኛ ሙሌት መጠናቀቁ  ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ የመልማት ፍለጎት እውን መሆን የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡

የግድቡ 3ኛ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ የመላው ኢትዮጵያውን የጋራ ጥረት ውጤት ማሳያ እና የትብብር ውጤት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የተፋሰሱን ሀገራት እና የአፍሪካ ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ በጋራ የመልማት እንጂ የተፋሰሱን ሀገራት የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ማሳወቋን አስገንዝበዋል፡፡

የግድቡ 3ኛ የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ ግድቡን ማጠናቀቅ አትችልም ለሚሉ ወገኖች ምላሽ የሰጠችበት ነው ያሉት አል አሩሲ፥ ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በማለፍ ግድቡን ጥቅም ላይ ማዋል እንደምትችል በተግባር አሳይታለች ብለዋል፡፡

3ኛው የውሃ ሙሌቱ መጠናቀቅ የአንደነታችን ውጤት ነው ያሉት አል አሩሲ፥ በቀጣይም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆም ብሄራዊ ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በከድር ሁሴን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.