Fana: At a Speed of Life!

የጎርፍ አደጋን በመከላከል በተለይም በዝናብ አጠር አካባቢዎች ጥቅም ላይ ለማዋል መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎርፍ አደጋን በመከላከል በተለይም በዝናብ አጠር አካባቢዎች ጥቅም ላይ ለማዋል መስራት እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ መከላከል ሥራዎች ሂደትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ እየተወያየ ነው።

የውሃና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች እየተፈተነች መሆኗን ገልጸዋል።

በዘንድሮው ዓመት በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰዋል።

በቅርቡም በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን እንዲሁም በአዲስ አበባ በደረሰ የጎርፍ አደጋም የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ንብረትም ወድሟል ብለዋል።

በቀጣይም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላና አፋር ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባና ሌሎችም በቀጣይ ከባድ ዝናብ ስለሚጠበቅ የጎርፍ አደጋን መከላከል እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የጎርፍ አደጋን በመከላከል በተለይም በዝናብ አጠር አካባቢዎች ጥቅም ላይ ለማዋል መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ለዚህም ማህበረሰቡና በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ የጋራ መፍትሄ በመፈለግ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.