Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገለፁ፡፡
አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለጣቢያችን በሰጡት አስተያየት ካርዳችንን ተጠቅመን ይመራናል ብለን ያሳብነውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
መምረጥ ማለት የራስ መብት ነው ያሉት ነዋሪዎቹ በዚህም በመጪው ሰኞ ድምፃችንን ሰጥተን የሚመራንን ፓርቲ እንመርጣለን ብለዋል፡፡
የተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ገዢው ፓርቲ ያደረጉት የቅስቀሳ መርሃ ግብርም ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ግንዛቤ የወሰዱበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዳግማዊ ዴክሲሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.