Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ካቢኔ ተበተነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ካቢኔ ተበተነ።

ካቢኔው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ መበተኑ ተገልጿል።

ፑቲን ለሃገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ሃገራቸው የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

የእርሳቸውን ንግግር ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ሙሉ ካቢኔያቸውን መበተናቸውን አስታውቀዋል።

አዲሱ የፑቲን እቅድ የሩሲያን የመንግስት አስተዳደር ከፕሬዚዳንታዊ ወደ ፓርላማ የሚቀይር ነው ተብሏል።

እቅዱ ፑቲን ተጨማሪ የስልጣን ጊዜ እንዲያገኙ ያስችላቸዋልም ነው የተባለው።

የህገ መንግስት ማሻሻያው መቸ እንደሚደረግ ግን አልተገለጸም።

የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት እና ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በቀጣይ ፑቲን በሊቀ መንበርነት በሚመሩት የሀገሪቱ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል በመሆን እንደሚያገለግሉም ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን የተበተነው ካቢኔ አዲስ ካቢኔ እስከሚዋቀር ድረስ በስልጣን እንዲቆይ ጠይቀዋል።

የሩሲያ ህገ መንግስት የሃገሪቱ መሪ ሁለት የስልጣን ዘመን ብቻ በወንበር ላይ እንዲቆይ ይፈቅዳል።

ሜድቬዴቭ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2012 የሩሲያ ፕሬዚዳንት በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡- ቪ ኦ ኤና አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.