Fana: At a Speed of Life!

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ ፣አበባ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የጎንደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ፡፡
 
የሁለቱ ተቋማት ሠራተኞች በጎንደር ከተማ ጠዳ ቀበሌ በመገኘት ነው የዘመች ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል የሰበሰቡት፡፡
 
የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ዲን ዘመነ ሐብቱ ÷ ዛሬ በዘማች ቤተሰቦች ማሣ ላይ ያለውን ሰብል ለመሰብሰብ ከመገኘታችን በፊት የህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ የ400 ሺህ ብር የሕክምና እና ምግብ ነክ ቁሳቁስ ድጋፍም አድርገናል ብለዋል፡፡
 
የጎንደር መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ እንዳለው አስማማው በበኩላቸው ÷ በዘማች ቤተሰቦች ማሳ ላይ ከመገኘታቸው እና ሰብል ከመሰብሰባቸው ባሻገር በግንባር በመገኘት ለሠራዊቱ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የመድሃኒት ድጋፍ ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
 
የህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት የገለጹት ሥራ አስኪያጅ÷ “ነፍሱን ለሰጠን ዘማች አርሶ አደር ይህን ማድረግ ትንሹ እገዛ ነው” ብለዋል፡፡
 
ሰብላቸው የተሰበሰበላቸው ፣ ልጆቻቸው ለዘመቻ የሄዱ አርሶ አደሮች፣ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ በቀጣይም ልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን እነሱም ለመሄድ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
 
በዕለቱም ከግማሽ ሄክታር በላይ የጤፍ ሰብል መሰብሰብ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
 
በስንታየሁ አራጌ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.