Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያኑ ጠ/ሚ ጁሴፔ ኮንቴ ስልጣናቸውን ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ  ስልጣናቸውን ለቀቁ።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የያዙበት መንገድ በተመለከት ተችት ሲቀርብባቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ አስገብተው ተቀባይነት አግኝቷል።

በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስከአሁን ከ85 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።

ጁሴፔ ኮንቴ ባለፈው ሳምንት በታችኞቹ ምክር ቤቶች የማስተማመኛ ድምፅ ያገኙ ቢሆንም በሴኔቱ የአብለጫ ድምፅ ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።

ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ህጎችን ለማፅደቅ እና ውሳኔዎችን ለማሳለፍ አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል ብሏል ስካይ ኒውስ በዘገባው።

የጣሊያን ፕሬዚዳንት ሰርጆኦ ማታሬላ ከሌሎች የሀገሪቱ ፓርቲ አመራሮች ጋር በነገው እለት ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን ኮንቴ እስከዛው የባላደራ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲቆዩ በፕሬዚዳንቱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.