Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚነስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር  የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ የዋትስ አፕ እና የቴሌግራም  መረጃ መለዋወጫ  አበለጸጉ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 20፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የጤና ሚነስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን  የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስመልክቶ የዋትስ አፕ እንዲሁም የቴሌግራም መረጃ መለዋወጫ  አበለጸጉ።

በዚህም ህብረተሰቡ  በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኝ ለማገዝ እና ለግንዛቤ ማስጨበጫነት የሚረዳ ይሆናል ተብሏል።

እነዚህ የመረጃ መለዋወጫ አገልግሎቶች(ቦት) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን የመድረስ አቅም አላቸው ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ የኮቩድ 19ኝ ላይ መረጃ ለሚፈልጉ ትዮጵያውያን ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኙ  ያስችላልም ነው የተባለው፡፡

እነዚህ መረጃ የመስጫ ቦቶች ስለኮሮና ቫይረስ የህመም ምልክቶች፣ሰዎች መውሰድ ስለሚገባቸው የቅድመ የጥንቃቄ  ተግባራት እንዲሁም የቫይረን ስርጭትና አጠቃላይ ሁኔታን የተመለከተ ዜናና መረጃ በአማሪኛ ቋንቋ እንደሚያቀርብ ከጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.