Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በአለታ ወንዶ የችግኝ ተከላ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አለታ ወንዶ ወረዳ ኢትዮጵያን እናልብስ መርሀግብር የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

መርሃ ግብሩ ከክልሉ፣ ከወረዳውና ከከተማው ሀላፊዎችና ማህበረሰብ ጋር በመሆን መካሄዱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ከዚህ ባለፈም የተቸገሩ ወገኖችን ለመደገፍ ቤቶችን የማደስ እንዲሁም የከተማ ጽዳት መርሃግብር አካሄደዋል።

በተጨማሪም በአለታ ወንዶ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየተሰጡ ያሉ የድንገተኛ፣ የማዋለድ እና የጨቅላ ህጻናት ህክምና እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.