Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ ከፖፑሌሽን ፈንድ ተወካይ ዴኒያ ጋይል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፖፑሌሽን ፈንድ ተወካይ ዴኒያ ጋይል ጋር ተወያዩ፡፡
ኢትዮጵያ ከፈንዱ ጋር ያላትን የረዥም አመታት ትብብር ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡
በስነተዋልዶ፣ የእናቶች እና የወጣቶች ጤና እንዲሁም የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ከፈንዱ ጋር ትሰራለችም ነው ያሉት፡፡
የትግራይ ክልልን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም በትብብር ለመስራት ተወያይተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.