Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በድምቀት መከበር የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃንን የተዛባ ዘገባ ያጋለጠ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በሀገራችን በድምቀት መከበሩ የአንዳንድ የምዕራባውን መገናኛ ብዙሃንን የተዛባ ዘገባ የሚያጋልጥና የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም በሚገባ ያሳየ ነው ሲሉ ጥምቀትን በኢራንቡቲ ያከበሩ ዲያስፖራዎች ተናገሩ።

በአሜሪካና በካናዳ ረጅም አመታትን ኖረው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ወደ ሀገራቸው የመጡት አቶ ኤርሚያስ መኮንንና ወጣት ሄርሜላ ተድላ፥ ጥምቀትን በሀገራቸው በተለይም በኢራንቡቲ በድምቀት በማክበራቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የውጭ ሀገራት ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ እዳይገቡ ጫና ቢበረታም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ግን ጫናውን ችላ ብለው ጥምቀትን በድምቀት ማክበር ችለናል ነው ያሉት።

ይህን የአለም ቅርስ ጭምር የሆነውን የጥምቀት በዓል በድምቀት ማክበራችን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አገራችን ሰላም መሆኗን በሚገባ ያሳየ ነው ያሉት ዲያስፖራዎቹ፥ በኢራንቡቲ ያለውን የጥምቀት አከባበርም በሚገባ ከማስተዋወቅ ባሻገር ኢትዮጵያ ፍጹም ሰላም መሆኗን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

44 ታቦታት በአንድ ስፍራ የሚያርፉበት የኢራንቡቲ አምሳለ ዳግማዊ ዮርዳኖስ ጥምቀተ ባህር ከከተራ ጀምሮ በድምቀት እየተከበረ ሲሆን፥ ዛሬ በቃና ዘገሊላ በዓል ይጠናቀቃል ።

በአበበ የሸዋልዑል

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.