Fana: At a Speed of Life!

የጦር መሣሪያ ምዝገባ ለ15 ቀናት ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ በሁሉም የአገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባ መራዘሙን አስታወቀ።

ዕዙ ከዚህ በፊት ባወጣው መመሪያ መሠረት የጦር መሣሪያዎች የምዝገባ ሁኔታን መገምገሙን አስታውቋል።
በግምገማው መሠረት ብዙ መሣሪያዎች በየክልሉ የተመዘገቡ መሆኑን በመመልከት ኅብረተሰቡና የጸጥታ ኃይሎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

የኅብረተሰቡን የተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ከዚህ በፊት የወጣው ትዕዛዝ የገጠር አካባቢዎችን ባለማካተቱ የተነሣ የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ዕዙ አምኗል።

በመሆኑም በሁሉም የአገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባው እንዲቀጥል መወሰኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል።

በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ጽህፈት ቤቶችም ይሄንን መመሪያ እንዲያስፈጽሙ መታዘዛቸውን ገልጿል።

ይህ መመሪያ በጦር ግንባር የዘመቱና የሚታወቅ የጸጥታ ኃይል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን እንደማይመለከትም ነው የገለጸው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.