Fana: At a Speed of Life!

የፀረ ወባ መድኃኒት የኮሮና ቫይረስን ለማከም ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፀረ ወባ መድኃኒት የኮሮና ቫይረስን ለማከም ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት ለሆነው የኮሮና ቫይረስ  መድኃኒት ለማግኘት የበርካታ ሀገራት ተመራማሪዎች ምርምር በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

በዚህ መሰረትም በቻይና ብቻ በበሽታው መድኃኒት ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ከ80 በላይ የቤተ ሙከራ ማዕከላት ተቋቁመው ስራ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

እነዚህ የቻይና ተመራማሪዎች ለወባ በሽታ መድኃኒትነት የሚያገለግለው “ክሎሮኪን ፎስፌት” የተሰኘው መድኃኒት የኮሮና ቫይረስን ለማከም ውጤታማ መሆኑን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

መድኃኒቱ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ በስፋት አገልግሎት ላይ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል።

በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውኃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና በሽታ አድማሱን በማስፋት በተለየዩ የዓለም ሀገራት ውስጥ እየተዛመተ ይገኛል።

አሁን ላይ በቻይና ብቻ ከ1 ሺህ 770 በላይ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 70 ሺህ 548 ማሻቀቡን  የቻይና ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ሺንዋ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.