Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ የኮቪድ19 ክትባትን ለማዳረስ ዓለም አቀፍ ድጋፉን ማሳደግ እንደሚገባ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ለአፍሪካ ሃገራት የኮቪድ19 መከላከያ ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ድጋፍ መጨመር እንደሚገባ አስታወቀ፡፡
አፍሪካ እስካሁን ድረስ ዓለም ላይ ከሚሰጡ የኮቪድ19 ክትባቶች ክትባቶች 2 በመቶውን ብቻ መቀበሏ ተገልጿል፡፡
በዚህም በዓለም ከተሰራጨው1 ነጥብ 4 ቢሊየን የኮቪድ19 ክትባት ውስጥ አፍሪካ 24 ሚሊየኑን ብቻ መውሰዷን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ውስን አቅርቦት እና በቂ ያልሆነ ድጋፍ አህጉሪቱ ከቫይረሱ መልሶ ለማገገም በምታደርገው ሂደት ላይ እክል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡
“ጥራት ያለው ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ውጤታማ እና አቅምን ያገናዘበ የኮቪድ19 ምርመራ፣ ህክምና ፣ የመድሃኒቶች እና ክትባቶች ፍትሃዊ ተደራሽነት” እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ በአፍሪካ 4 ሚሊየን 759 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየን 286 ሺህ 376 ሰዎች አገግመዋል፡፡
127 ሺህ 596 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ ፦ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.