Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በፈረንጆቹ 2020 ሁለተኛ ሩብ አመት በ13 ነጥብ 8 በመቶ ቀንሷል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት በፈረንጆቹ 2020 ሁለተኛ ሩብ አመት በ13 ነጥብ 8 በመቶ መቀነሱን የሃገሪቱ ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ለሃገር ውስጥ ምርት እድገቱ መቀነስ ምክንያት መሆኑንም ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

በሃገሪቱ በሁለተኛ ሩብ አመት የተመዘገበው ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት ከተተነበየው እጅጉን የተሻለ ቢሆንም ከአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት የሃገር ውስጥ ምርት እድገት አንጻር ግን የከፋው ነው ተብሏል፡፡

የፈረንሳይ ጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት እድገት የአሁኑን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ሩብ አመት ቅናሽ አሳይቷል፡፡

እንደ ቢሮው መረጃ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት የመጨረሻ ሩብ አመት ላይ በ5 ነጥብ 3 እንዲሁም በ2020 የመጀመሪያ ሩብ አመት ደግሞ በ5 ነጥብ 9 በመቶ ቀንሷል፡፡

ይህም የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ክፉኛ እያሽቆለቆለ መሆኑን እና ድቀት ላይ መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.