Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እና የኢቢሲ አመራሮች በከተማዋ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኝተዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እና የኢቢሲ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኝተዋል።

አመራሮቹ የመስቀል አደባባይ-ማዘጋጃቤት ፣አድዋ ፕሮጀክቶችና የሸገር ቤተመጻህፍትን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ኢ/ር ታከለ ኡማ ለመገናኛ ብዙሀን አመራሮቹ ፕሮጀክቶቹን አስጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ የመገናኛ ብዙሀን በከተማዋ እየተገነቡ ስላሉ ፕሮጀክቶች አስፈላጊው መረጃ እንዲኖራቸውና በተገቢው መልክ ለህብረተሰቡ መረጃው እንዲደርስ ለማገዝ ነው፡፡

የመገናኛ ብዙሀን አመራሮቹ ባዩት የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በፕሮጀክቶቹ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ በማድረስና በተለያዩ መልኩ ለማገዝ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.