Fana: At a Speed of Life!

የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ ምርት ወደ መዲናዋ መግባት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ንብረትነቱ የአቶ በላይነህ ክንዴ የሆነውን የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ የሚያመርተውን ዘይት  ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምሯል።

የፌቤላ የፓልም ዘይት ፋብሪካ  ለአዲስ አበባ ከፋብሪካው ምርት በወር 3 ሚሊየን ሊትር ዘይት ለማቅረብ   ስምምነት የተፈጸመ መሆኑን የመዲናዋ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ከስምምነቱ 3 ሚሊየን ሊተር ዘይት ውስጥም እስካሁን 120 ሺህ  ሊትር ዘይቱን ቢሮው መረከቡን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በመጋዘን ያለውን ክምችት በማሳየት ገልጸዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት መጋዘን ተገኝቶ ባለ 20 ሊትር የፌቤላ ዘይት ፋብሪካ ምርት የሆኑ ዘይቶች መግባታቸውን አረጋግጧል።

በቀጣይ የሚገቡት ዘይቶችም ለህብረተሰቡ ምቹ እንዲሆኑ ባለ 3 እና ባለ 5 ሊትር እሽጎች እንደሚሆኑ ስምምነት መፈጸሙንም ቢሮ ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

ሰሞኑን በህገወጥ መልኩ ተከማችተው የተገኙ በርካታ የዘይት ምርቶችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የሚናገሩት ቢሮ ሃላፊው ÷በሀገር ውስጥ የተመረቱትና በህጋዊ መልኩ ከውጭ የሚገቡት የሱፍ ዘይቶች ተጨማምረው የህብረተሰቡን ፍላጎት የመድረስ አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከነገ ጀምሮ ወደ ህብረተሰቡ በሸማች ማህበራት በኩል መከፋፈል የሚጀምሩት የዘይት ምርቶቹ የስርጭት ችግር እንዳያጋጥማቸው ከክፍለተሞችና ከሸማች ማህበራት ጋር በቂ ዝግጅትም ተደርጓልም ነው ያሉት።

የፌቤላ የፓልም ዘይት ፋብሪካ ለጋምቤላ ክልልም 780 ሺህ ሊትር ዘይት ለማቅረብ ስምምነት መፈጸሙን የኢንደስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ገብረ ማርያም  ተናግረዋል።

የድሬዳዋ የሸሙ ዘይት ፋብሪካው አሁን ላይ ማምረት ከጀመረው የዘይተ ምርት 780 ሺህ ሊትር ለሶማሌ ክልል በማቅረብ በአካባቢው  ያለውን ፍላጎት ለመድረስ እየተሰራ መሆኑንም ነው አቶ ንጉሴ ገልጸዋል።

በትእግስት ስለሺ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.