Fana: At a Speed of Life!

የፌደራልና የክልል መንግሥታት በሀገሪቱ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን አስመልክቶ መንግሥት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ገመገሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል እና የክልል መንግሥታት አመራሮች በሀገሪቱ በርካታ ክልሎች ያጠቃውን የተፈጥሮ አደጋ አስመልክቶ መንግሥት የወሰዳቸውን እርምጃዎች መገምገማቸው ተገለጸ።

ግምገማውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ግምገማውን አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ቢከሠትም፣ ምንም ዓይነት የሞት አደጋ አለመድረሱ መልካም መሆኑን ነው ያነሱት።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ተገኝቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተከታታይ በተደረጉ ውይይቶች በሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የሚከናወኑ እርዳታዎችን ጨምሮ፣ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

በውይይታቸው አልፈው አልፈው የሚነሡትንና የዜጎችን ሕይወትና ንብረት እየነጠቁ ያሉትን የጸጥታ እክሎችን አስመልክቶም መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይም በድንበር አካባቢ የሚፈጠሩት ክሥተቶች፣ የለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ በሚሹ ቡድኖች የሚቀናበሩ መሆናቸውንም አንስተዋል።

በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሚመራው ተልእኮ ይከናወናልም ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የታገቱት 29 ሰዎች እንዲለቀቁ ጥረት ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ” ሲሉ ገልፀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.