Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራልና ክልሎች ኢንቨስትመንት ተቋማት የ2014 የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራልና ክልሎች ኢንቨስትመንት ተቋማት የ2014 የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ በጅግጅጋ ተጀመረ፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ፣ የሶማሊ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ-ኑር፣ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዛይነብ ሃጂ አዳም እና ሌሎች የፌዴራልና ክልል ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በዚህ ወቅት÷ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማደግ፣ የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚገኙ ባንኮችንና ስራ እድል ፈጠራን በመጠቀም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልዩ ትኩረት መስጠቱንና ኢንተርፕራይዞችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በግምገማው ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ እና ምክትል የቢሮ ሃላፊዎች ÷ የቢሮው የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ÷ በዘርፉ መሻሻል ስለሚገባቸው ነጥቦችና መቀጠል ያላባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ግምገማው በኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በተለይ በግብርናና እንስሳት እርባታ ዘርፉ እንዲሁም ባለሃብቶችና ዳያስፖራው በኢንዱስትሪና አገልግሎት ሰጭ ዘርፉ ያከናወኑት የኢንቨስትመንት ሥራዎች ደካማና ጠንካራ ጎኖች የታዩ ውጤቶች እንዲያተኩር የሶማሌ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ-ኑር መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.