Fana: At a Speed of Life!

ልዩ ድጋፍ የሚሹና ያልለሙ አካባቢዎችን በተሻለ መልኩ መለወጥ የሚያስችል የሦስት ዓመት ዕቅድ ይዘጋጃል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአቅምና የልማት ክፍተት በሚታይባቸውና ልዩ ድጋፍ በሚሹ አካባቢዎች የተሻለ ልማት ለማምጣት የሦስት ዓመት ዕቅድ የሚዘጋጅ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ቦርድ አባላት የቦርዱን የ2011/12 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምና የ2013 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው በዚሁ ውይይት ላይ የእቅድ አፈጻጸሙን ያቀረቡት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን “ቦርዱ በአሥር ዓመታት ቆይታው በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ካሉበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የሚጠበቀውን ያህል ለውጥ ሊያመጡ የሚያስችሉ ተግባራት እንዳልተከናወኑ አንስተዋል።

በተለይ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ የጸጥታ ችግሮች  የእቅዱን አፈጻጸም እንዳጓተቱት ተናግረዋል።

በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ አጎራባች ክልሎችም ቢሆኑ በጎንዮሽ ትስስር አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ረገድ ውስንነት እንደነበረባቸው ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት።

“የክፍተቶቹ ድምር ውጤት ደግሞ በግብርና ዘርፍ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በሲቪል ሰርቪስና መንገድን በመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች የሚጠበቀው ውጤት እንዳይመዘገብ አድርጓል” ሲሉ አብራርተዋል።

የፌዴራል ልዩ ድጋፍ ቦርድ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎችን በተሻለ መልኩ ለመለወጥ የሦስት ዓመት እቅድ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።

የእቅድ ዝግጅቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከመጪው ጥር ጀምሮ ወደ ትግበራ እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.