Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማሻሻልን ዓላማ ያደረገው 12ኛው የፌዴራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ጉባኤ በአዳማ ተካሄደ።

ጉባኤው በለውጥ መርህ በተቃኘ አስተሳሰብና በሙያዊ ስነ ምግባር በመታገዝ የህግ ታራሚዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የማረምና የማነፅ አገልግሎትን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም “ማረሚያ ቤቶች የህግ ታራሚዎች ሰብአዊ መብቶች የተከበሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ ተግተን እንሰራለን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው፡፡

የክልልና እና የከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ፤የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በጉባኤው እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.