Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል 6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ያቀረቡትን በጋራ ክልል የመመሰረት ጥያቄ ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ስር የሚገኙ 6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ያቀረቡትን በጋራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመመሰረት ጥያቄ ላይ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
 
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደው ባለው አስቸኳይ ስብሰባ ከቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አስቀድሞ በማንነት አስተዳደር እና የወሰን ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል በደቡብ ክልል10 ዞኖችአቅርበው ስለ ነበረው በተናጠል እንደራጅ ጥያቄ እና ይህንኑ መሰረት በማድረግ ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ቀርቧል፡፡
 
በዚህም የክልልነት ጥያቄ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ ቢቆዩም በተለይም ባለፉት 3 ወራት ዝርዝር የዳሰሳ እና መነሻ ሃሳብ እንዲቀርብ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
 
በመነሻ ሃሳቡ በወጡት እቅዶችውስጥ መሰረታዊ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡
 
በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ጥያቄዎቹን የህዝብን ጥቅም በሚያስከበር መልኩ መልስ እንዲያገኙ ማድረግ እና ዞኖች ከተናጠል ይልቅ በክላስተር ቢደራጁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚኖረው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
በተጨማሪም በሁለት ክልል እንዲደራጁ የሚል ሀሳብ የቀረበ ሲሆን፥ ይህንን ለማከናወን የሚያስፈልጉ መርሆች ማዘጋጀትም ሌላኛው ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
በሀይለየሱስ ስዩም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.