Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር በአዳማ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ውስጥ ከተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች ጋር በአዳማ እየመከረ ይገኛል፡፡

የምክክር መድረኩ የብሔር ብሔረሰቦች በዓልን በተመለከተ እየተዘጋጁ ካሉ የምክክር መድረኮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገር ሽማግሌዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ከስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በወረርሽኙ ምክንያት ህግመንግስቱን ያከበሩ ህጋዊ አካሄዶችን በመንተራስ ሃገራዊ ምርጫው እንዲራዘም መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ የአገሪቱን ህገመንግስት ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔና በመጻረር ህወኃት ህጋዊ ያልሆነ ምርጫ በማካሄድ ህገወጥ ካቢኔ መመስረቱን አስረድተዋል፡፡

በሃገሪቱ ውስጥ በሚካሄደው ህገወጥ ተግባራት ጀርባ ያለው ይህ ቡድን ይህ አልበቃው ብሎ የኢትዮጵያ ምልክት በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙንም አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት ውሳኔ ማሰፉን ነው የገለጹት፡፡

መንግስት ይህን ቡድን ለህግ ለማቅረብ እየወሰደ ያለውን እርምጃ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች እንዲደግፉና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡

የሃገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው መንግስት እስከአሁን ያሳየው ትዕግስት ከበቂ በላይ ስለሆነ ለህዝቦች ደህንነትና ዋስትና ሲባል የትግራይ ህዝብ በማይጎዳበት መልኩ ወንጀለኛውን ቡድን ለህግ የማቅረብ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ወስነዋል፡፡

የሃገር ሽማግሌዎቹ መከላከያ ሰራዊት ህወኃት ውስጥ ባለው ቡድን ላይ እየወሰደ የሚገኘውንም እርምጃ እንደሚደግፉ ነው የገለጹት፡፡

 

በብዙዓለም ቤኛ

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.