Fana: At a Speed of Life!

የፍቺ ጥያቄ በ300 ፐርሰንት መጨመሩ እየተነገረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፍቺ ጥያቄ በ300 ፐርሰንት መጨመሩ ዘጋርድያን ትናንት ማምሻውን ዘግቧል፡፡

የፍቺ ጥያቄው በዚህ መጠን ሊጨምር የቻለው የኮሮና ቫይረስ ባስከተለው መዘዝ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ባልታየ መልኩ ሰዎች ስለ ስለሞት በእጅጉ ማሰብ እንደጀመሩም ተሰምቷል፡፡

ጥንዶች በቫይረሱ ምክንያት የተጣለው ገደብ አስመልክተው ጉዳያቸው በኦንላይን እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም ወደ አማካሪ ተቋማት የሚሄዱ ጥንዶች እንደጨመሩ የተናገሩት የስነልቦና ባለሙያው ከዚህ ቀደም በጥንዶቹ መካከል  ስምምነት ቢርቅ አንደኛው ከቤት በመውጣት እንደሚያሳልፉት አንስተው አሁን ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ አማካኝነት ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የፍቺ ጥያቄዎች ከወትሮ በተለየ ሁኔታ እየጨመሩ እንደመጡ ነው ያነሱት፡፡

የኦንላይን የገበያ እንቅስቃሴዎችም በተጣለው ገደብ ምክንያት ትርፋማ እየሆኑ ነው ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.