Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያን ህልውና በመጠበቅ ረገድ የጋራ አቋም መያዝ ይጠበቅባቸዋል – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫው የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያን ህልውና በመጠበቅ ረገድ የጋራ አቋም ይዘው መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው አንጋፋው ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ።

“ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ብትሆንም ምርጫው መካሄዱ ትክክለኛና ተገቢ ነው” ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ በምርጫው የሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን የፖሊሲ አማራጭ አቅርበው ማሸነፍ የሚችሉት በቅድሚያ የአገር ህልውና ተጠብቆ ሲቀጥል ነው።

በመሆኑም ፓርቲዎቹ የኢትዮጵያን ህልውና በሚመለከት የጋራ አቋም ይዘው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎች እየተከናወኑ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ ጠቁመው÷ ችግሮቹን መፍታት የሚቻለው በጋራ በመስራት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ህልውና ከማይፈልጉ የውጭ ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው አገር የማተራመስ ስራ እየሰሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ያብራሩት አቶ አንዳርጋቸው ÷ ይህም ያለንበትን ወቅት እጅግ ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል።

ከዚህ አንጻር 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ አገርን የማፍረስ ሳይሆን አገርን የማዳን ዓላማ የያዘ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜጎች ኢትዮጵያ አሁን የተጋረጠባትን ፈታኝ ጊዜ በድል ለማለፍ በጋራ እንዲቆሙም አቶ አንዳርጋቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.