Fana: At a Speed of Life!

የ103 ዓመቱ አዛውንት ከ27 አመቷ ወጣት ጋር ጋብቻ ፈጽመዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ27 ዓመት ወጣት ሴት ጋር ትዳር የመሰረቱት የ103 ዓመቱ አዛውንት አነጋጋሪ ሆነዋል።

በቅርቡ በኢንዶኖዥያ ደቡብ ሱላወሲ ግዛት አንድ የ103 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ የ27 ዓመቷን ወጣት በደማቅ የሰርግ ስነ ስርዓት ማግባታቸው ተሰምቷል።

የሰርግ ስነ ስርዓቱን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መለቀቁን ተከትሎም ብዙዎች ተቀባብለውታል።

በምስሉ የ103 ዓመቱ አዛውንት በሰዎች ተደግፈው ከ27 ዓመቷ ወጣት የትዳር አጋራቸው ጋር የተለያዩ የሰርግ ስነ ስርዓቶችን ሲያከናውኑ ይታያሉ።

በመካከላቸው የ76 ዓመት የዕድሜ ልዩነት ባላቸው ሁለት ጥንዶች የተመሰረተው ይህ ጋብቻ በሀገሬው ሰዎች ዘንድ አግራሞትን አጭሯል።

ከዚህ በፊት በሀገሪቱ የ76 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አዛውንት ከ16 ዓመት ታዳጊ ጋር ትዳር መመስረታቸው በዘገባው ተመላክቷል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.