Fana: At a Speed of Life!

የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ መራዘሙን ካፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈንጆቹ ከሰኔ 23 ቀን 2023 እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2023 ድረስ በኮትዲቯር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ መራዘሙን ካፍ አስታውቋል፡፡
የካፍ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፓትሪስ ሞሴፔ በዛሬው እለት እንዳስታወቁት÷34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮትዲቯር ባለው የአየር ሁኔታ ምክንያት በታቀደለት መርሐ ግብር እንደማይከናወን ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንጆቹ 2024 ጥር እና የካቲት ወራት የሚካሄድ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አስታወቀዋል፡፡
የካፍ ኮንግረስ በዋናነት ጨዋታውን ስለማራዘም መወያየቱን ገልጸው÷ የማጣሪያ ጨዋታ ቀናት በቀጣይ ይፋ ይደረጋሉ ማለታቸውን የካፍ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.