Fana: At a Speed of Life!

የ21ኛው ዙር  “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ፣ይሸለሙ” የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 21ኛው ዙር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ”ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ” የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ በተከናወነው የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብር ላይም የባንኩ ከፍተኛ  የስራ ሀላፊዎች ፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

በዚህም  ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው አንደኛው እጣ ቁጥር 7968156 ሆኗል ።

ሁለተኛው እጣ ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን የሚያስገኙ የእጣ ቁጥሮች 7969118 እና 7959825 ሆነው ወጥተዋል።

በሶስተኛ ዕጣ 20 ላፕቶፖች የሚያስገኙ የዕጣ ቁጥሮችም  መውጣታቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.