Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሐረሪ፣ ሲዳማ እና ሶማሌ ክልሎች እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሐረሪ፣ ሲዳማ እና ሶማሌ ክልሎች መስጠት ተጀምሯል።

ፈተናው በሶስቱም ክልሎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን ድረስ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በሐረሪ ክልል 4 ሺህ 213 ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ መቀመጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው ደንብ እና መመሪያ መሠረት የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

በሲዳማ ክልል 81 ሺህ 277 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ፈተናው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ አስፈላጊው ጥንቃቄ ታክሎበት እንደሚሰጥ ኢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.