Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ መሰጠት ጀመረ 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች 73 ሺህ 45 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ፈተና እየወሰዱ ነው፡፡

ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ ባዮሎጂ ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ የህብረተሰብ ሳይንስ፣ ሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርቶች ናቸው፡፡

በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች የአማርኛ እና የእንግሊዘኛ ትምህርቶችን ፈተና በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ ሲሰጥ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎችም እስከ ታህሳስ አጋማሸ ድረስ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.