Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ወደ መቐለ እና ማይፀብሪ ምግብና የህክምና አቅርቦቶች መላኩን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት ወደ መቐለ እና ማይፀብሪ 8 ሺህ ያህል ካርቶን ምግብና የህክምና አቅርቦቶች መላኩን ገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ 2 ሺህ 700 ሃይል ሰጪ ብስኩቶችን ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡር ለሆኑ እናቶች እና ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች ወደ ስፍራው መላኩን አስታውቋል፡፡
በትግራይ እና አማራ ክልሎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሚያስከትለውን መዘዝ ለማስወገድም አስፈላጊ አቅርቦቶችን ለሁሉም ማዕከላት ማድረስ አስፈላጊ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.