Fana: At a Speed of Life!

ዩ ትዩብ የተሳሳቱ ያላቸውን በኮቪድ -19 ክትባት ዙሪያ የተጫኑ ቪዲዮዎችን አገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዩ ትዩብ የተሳሳቱ ያላቸውን የኮቪድ-19 ክትባት ዙሪያ በገጹ የተለቀቁ ንቀሳቃሽ ምስሎችን አገደ።

በቀጣይም በኮቪድ -19 ዙሪያ የተሳሳተ መረጃን ለመከላከል ኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን በተመለከተ የሚለቀቁ የተሳሳቱ ተንቀሳሰቃሽ ምስሎችን ከገፁ ለማጥፋት ቃል መግባቱም ነው የተገለጸው።

ከብሔራዊ የጤና አገልግሎት፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና የአካባቢው የጤና ተቋማት ምክርን የሚቃረኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከዩ ትዩብ የሚጠፉ እንደሆነም ነው የተነገረው።

በፌስቡክ ሰዎች ክትባት እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ማስታወቂያዎችን እንደሚያግድ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው ዩ ትዩብ የኮቪድ-19 ክትባት ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያገደው።

ሆኖም ገደቡ ያልተከፈለባቸው ልጥፎችን (ፖስቶችን) ወይም አስተያየቶች ላይ ተግባራዊ እንደማይሆንም ነው የተገለጸው።

በአሁኑ ወቅት ክትባቱን የሚመለከቱ የተሳሳተ ይዘት ያላቸውን በእገዳው ለማካተት ፖሊሲውን በግልጽ እያሰፋ ማምጣቱን የሚያመለከት ነው ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.